Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Saturday 26 May 2012

ሙስሊሞች ላይ እየተፈጸመ ያለውን በደል ቅዱስ ሲኖዶስ በማውገዙ ሙስሊሞች ምስጋናቸውን ገለጹ

ግንቦት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በስደት የሚገኘው የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ በ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ እየተፈጸመ ያለውን በደል በማውገዙ አድናቆታቸውን እና ምስጋናቸውን ገለጹ።
በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ 33 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ሲያጠናቅቅ የ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች ህገ-መንግስቱ በፈቀደላቸው መሰረት እምነታቸውን በነፃነት እንዳይከተሉ መንግስት ጣልቃ በመግባት እየፈጠረባቸው  ካለው ጫና  በ አስቸኳይ እንዲቆጠብ መጠየቁ ይታወሳል።
ከዚህም በላይ በአርሲ -አሰሳ የመብት ጥያቄ ባነሱ ሙስሊሞች ላይ የተፈጸመውን ግድያ አጥብቆ ያወገዘው ሲኖዶሱ፤ “ስለራሳችን ብቻ ሳይሆን ስለሙስሊም ወንድሞቻችንም እንጮኻለን” በማለት አጋርነቱን መግለፁ ይታወሳል።
ትናንት በአወሊያ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ የዋሉ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ሙስሊሞች   በ አቡነ መልከ ጼዴቅ አማካይነት ለተላለፈው የ አጋርነትና የወንድምነት መግለጫ አድናቆታቸውንና ገልፀዋል::
ኢትዮጵያ፤ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች ለዘመናት  በልዩ ሁኔታ ተዋደው እና ተከባብረው የሚኖሩባት የዓለማችን  አገር መሆኗ በስፋት ይነገራል።
በትናንትናው ተቃውሞ ላይ የሙስሊም አመራሮች የተለያዩ ንግግሮችን ሲናገሩ መደመጣቸው፣ የአወሊያ መሪዎች ምናልባት ለወደፊቱ ስለሚከተሉት መንገድ አቋም አልያዙም ይሆን የሚል ጥያቄ አስነስቷል። አንዳንድ መሪዎች ነጻነታችን በጠየቅን፣ አሸባሪ ተባልን ሲሉ እና ትግላቸው የመብት ጥያቄ መሆኑን ሲገልጡ፣ ሌሎቹ ደግሞ ተቃዋሚዎች ጥያቄያቸውን ከሀይማኖት አውጥተው ሰፋ አድርገው እንዲመለከቱ ጫነ እያደረጉባቸው መሆኑን ተናግረዋል። በአወልያ የተጀመረው እንቅስቃሴ ያለምንም መፍትሄ አምስተኛ ወሩን ለመያዝ ቢቃረብም እስካሁን ከመንግስት በኩል የተሰጠው መልስ አላረካንም በሚል ሙስሊም ኢትዮጵያዊ ተቃውሟቸውን እንደቀጠሉ ነው።

No comments:

Post a Comment