Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Monday 7 May 2012

በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ባስነሱት ተቃውሞ በርካቶች ታስረዋል

ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ተቃውሞው ምግብን ሰበብ አድርጎ እንደተፈጠረ ቢነገርም፣ የተማሪዎች ግን ከዚህ የዘለለ ነው ተብሎአል። ትናንት ከሰአት በሁዋላ የተነሳው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ተቃውሞው ከዞኑ ፖሊስ አቅም በላይ በመሆኑ የፌደራል ፖሊስ ጣልቃ ገብቷል። ተማሪዎች በፖሊሶች ላይ የሚያወርዱት ድንጋይ  መምህራኑ ከግቢያቸው እንዳይወጡ አድርጓቸው እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የፌደራል ፖሊስ ግቢውን ለመቆጣጠር መሳሪያዎችን መተኮሱን አድማ በታኝ ጭስ መጠቀሙን ለማወቅ ተችሎአል። እስካሁን በግጭቱ ምን ያክል ሰዎች እንደሞቱ ለማወቅ ባይቻልም በርካታ ተማሪዎች ተይዘው መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። በተቃውሞውም በዩኒቨርስቲው ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። ይህን ዜና እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው።
ከአዲስ አበባ ወደ 300 ኪሜ የሚርቀው ደብረማርቆስ የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ነው።
በሌላ ዜና ደግሞ በምእራብ ጎጃም ዞን ከውሀ ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት ሰዎች ተገደሉ
ከውሀ ጠለፋ ጋር በተያያዘ በይስማላ እና ሊበን በሚባሉ ሁለት የምእራብ ጎጃም አካባቢዎች የተነሳው ብጥብጥ  የ 3 ሰዎችን ህይወት ሲቀጥፍ ፣ በርካቶች ደግሞ  ቆስለዋል። ግጭቱ በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ሲነገር ፣ ባህርዳር ከተማ የነበረው የፌደራል ፖሊስ ወደ አካባቢው በመሄድ ግጭቱን መቆጣጠሩን ለማወቅ ተችሎአል። ፈጥኖ ደራሽ ፖሊሶችም ግጭቱን ቀስቅሰዋል ያሏቸውን ከ40 በላይ ሰዎች ይዘው አስረዋል።

No comments:

Post a Comment