Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Saturday 12 May 2012

እየሩሳሌም ሆይ ተነሽ!!!....ተላከ ከእስራኤል

እምነቴና ዘሬም በሙሉ ይሁዲ፡ ሙሉ በሙሉ እሥራኤላዊ ብሆንም፡ ምንም ቢሆን 2500 ዘመንም የአያት
የቅድመ አያቴ አጽም፤የእኔም ሆነ የልጆቼ እትብት የተቀበረባት ሃገረ ኢትዮጵያ በመሆኗ ፤"ባይቆጭ
ያንገበግባል" ይሉ የለም አበው !!!
ምንም እንኳን አንድ ቀን ከፈለስንባት ቅድስት ሃገራችን እንመለሳለን የሚለው ህልም ዕውን እስኪሆን ድረስ!
የእኛም አያት ቅድመ አያት፤ አባቶች፤እናቶች፤ወንድሞች፤ እህቶችና ልጆች ለዚህች ኢትዮጵያ ለምትባል ሃገር
እንደማንኛውም የሃገር አንድነት ወዳድ ኢትዮጵያዊ አብሮ በመዝመት ከውጭ ወራሪና ከውስጥ ቦርቧሪ ጋር
በመፋለም፤ ክቡር ህይወቱን አሳልፎ አንገቱን ለሰይፍ ደረቱን ለጥይት ሰጥቶ ህይወቱን ሰውቷል!! ከዚያም
ባሻገር፤ ከኋላ ደጀን በመሆን የተበላሹ የጦር መሳረያዎችን እየጠገነ ለተዋጊው የህዝብ ሰራዊት በመመለስ
ተዋግቷል! አዋግቷል !!
ታዲያ ከዚህ ከወደ እሥራኤል ስለ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ይዘት፤ የማህበራዊ ኑሮና የኢኮኖሚ ሁኔታ ግድ የለሽ
መሆን ስላስገረመኝ ነው። እኔ ከፍ ብየ እንደገለጽኩት አንድም የኔ ዘመድ የሆነ ሰው በኢትዮጵያ ምድር
አልቀረም። ምንም እንኳን በተለያዩ ነገሥታትና መንግሥታት ለህዝቧ ነጻነትና መብት ብዙም ግድ
ባይኖራትም፡ ይሁዳውያን ግን ድርብ ተደራራቢ በሆነ ጭቆና ከሌላው ኅብረተሰብ ተለይተው ተዋርደውና
ህልውናቸው ተረግጦ ይኖሩ ከነበረው ወጥተው፤ አሁን እዚህ እሥራኤል በነጻነት ሲኖሩ፤ እንዴት ነጻነት
ለጠማው ህዝብ ጩኽቱን ማሰማት ተሳናቸው?! የመብት ረገጣና የነጻነት ማጣት ሰቆቃው ምን ያህል አስከፊ
መሆኑን! አሁን ከዚህ በነጻነትና ሙሉ መብቱን ለማስጠበቅ የተመቻቸ የዲሞክራሲ መርህ ካለው ህዝብ የበለጠ
ማን ይረዳዋል !!
እንደ ኢሮ.አ.ቆ በ-1991 በኦፕሬሽን ሽልሞ(የሰለሞን ዘመቻ) በሚባለው ቢያንስ በግምት ወደ አንድ እጅ
ከመቶው የመጣው ከይሁዳውያን ጋር የተጋቡና የተዋለዱ በመሆናቸው፤ ከዚያ በኋላ እስካሁን የሚመጣው
አብዛኛው በስመ ይሁዲ ሲሆን የሚበዙት ምንም የይሁዲ ዘር የሌላቸው በተለያየ አጋጣሚ የሚመጡ ዜጐች፡
ግን መላው ቤተሰባቸው ኢትዮጵያ የሚገኝ ናቸው። ታዲያ እነሱ እንኳን ተነስተው ጩኽታቸውን የማያሰሙት
ለምን ይሆን?! ስለራሳቸው እንጂ ስለ ወገናቸው ግድ የላቸውም ማለት ነው !!
እንደ ኢሮ.አ.ቆ በ-2003 እና 2005 መለስ ዜናዊ መጥቶ በነበረበት ጊዜ እውነተኞቹ የኢትዮጵያ ስደተኞች
መለስ ዲክታተር! መለስ ሌባ! መለስ ነፍሰ ገዳይ!...ወዘተ እያሉ መፈክሮችን በመያዝ እየሩሳሌም በአረፈበት
"ኪንግ ደቪድ" በተባለው ሆቴል ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረጋቸው ሳቢያ በመናደድ፤ ከመንግሥትም ሆነ
ከእሥራኤላውያን ጋዜጠኞች ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ፦"ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንጅ የፖለቲካ ችግር የለም፡
ሁሉም ወደ ሃገሩ በመመለስ መኖር ይችላል ማንም አይፈልጋቸውም!!” ብሎ ከሄደ በኋላ፤ የሰላማዊ ሰልፉ
አስተባባሪ የሆኑት በጥቆማ ተይዘው በመታሰር፤ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱ የተወሰኑትን የበላ ጅብ እስካሁን
አልጮህ እንዳለና፤ የተወሰኑት እንደታሰሩ ወዲያውኑ በ human rights በኩል ሲሰማ፤ በተለይ በደርግ
መንግሥት ወታደር፤ የተለያዩ መኰንኖች እና አንዳንድ ከተለያዩ የሥራ ሃላፊነት በፖለቲካው ምክንያት
የተባረሩ ደግሞ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ለህይወታቸው አስጊ ነው ተብሎ የታመነባቸው ኢትዮጵያውያን
በየዓመቱ፤ የአንዳንዶች ደግሞ በየስድስት ወሩ የሚታደስ መታወቂያ ብቻ ተሰጥቷቸው የሚኖሩት በጣም በጣት
የሚቆጠሩ ናቸው።
እነዚህስ ኢትዮጵያ የሚሰቃዩትን ወገኖቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ሰቆቃ ምነው መጮህ ተሳናቸው?! እነዚህ
ቢዎጡ ለሰላማዊ ሰልፍ ደጋፊያችቸው ብዙ ነበር!! እዚህ ሃገር እኮ አንድ ሰውም ይሰማል ብቻውን ቢጮህ!
በተለይ በዚህ 15 ዓመታት እየሩሳሌምን ለመሳለም እየተባለ በፋሲካ የሚመጡት በአብዛኛው ወጣቶቹ ትግርኛ
ተናጋሪዎችና ትግሬዎች ሲሆኑ፤ አማርኛ ተናጋረዎቹ ግን ቁጥራቸው አነስተኛ ከመሆኑም ባሻገር እድሜዓቸው
ከ-55 በላይ የሆኑ ሽማግሌዎች ብቻ ናቸው።ይገርማል !!
መንግሥተ ሰማያትንም ትግሬዎችና ትግርኛ ተናጋሪዎች ብቻ እንዲገቡባት መለስ አዘዘ?!ጉድ ይሏል!!
ይገርማችኋል፤ እነዚህ ትግርኛ ተናጋሪዎች ወዲያው ጊዜ ሳይፈጅ የስደተኝነት የመኖሪያ ፈቃድ ተሰጥቷቸው
ታያለህ ትሰማለህ፤ በዚያ ላይ ይሁዳውያን የትግርኛ ተናጋሪዎች ጋር ግንባር ፈጥረው ማህበር በማቋቋም
የተለያዩ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ሲመጡ፤ በይሁዳውያኑ ትግሬዎች ስም ስብሰባ ይደረጋል። ከዚያ
ለልማት፤ለድርቅ፤ለደን መራቆት፤በጦርነት ለተጐዱ...ወዘተ እና በቅርቡ ደግሞ በየከተማው
በአሽቃቫጮቻቸው በኩል ይህን የዋህ ይሁዲ ይሰበስቡና የቦንድ አውጡ በማለት የዋሁ ይሁዲ በቅንነት
እውነትም ለኢትዮጵያ ልማት የሚውል እየመሰለው ያዋጣል።
ማን ያስረዳው!! ሬዲዮውም ሆነ ቴለቪዥኑ የአማርኛው፤ ሰኞና ማክሰኞ አምባሳደሩን ነው ቃለ መጠየቅ
የሚያደርጉ።ታዲያ ህዝቡ እውነቱን እንዴት ይወቅ?! አንዳንዶች ደፋሮች ደፍረው ሲናገሩ አንተ ስለኢትዮጵያ
ምን አገባህ ይባላሉ!! አንተ እሥራኤላዊ ነህ!ቅስማቸው ይሰበራል!! ዝም!! ዝም !!
የስደተኝነት መታወቂያ ያላቸው ትግሬዎችም ከአምባሳደሩ ጋር እየተገናኙ፤ህዝቡን እንዲቀሰቅሱ ይላካሉ።
እያንዳንዱ ምን ያህል ገንዘብ ሰበሰበና እንዴት መሰብሰብ እንዳለበት ይወያያሉ። ከዚያ በዚያ መከረኛ ራዲዮና
ቴሌቪዥን ይህን ያህል ዶላር እሥራኤል ከሚገኙት ቤተ-እሥራላውያን ተሰበሰበ ነው ቅስቀሳው!!
እውነተኞቹ ስደተኞች ደግሞ ተደብቀውና እነዚህን የመለስን ተላላኪዎች እንዳይጠቁሟቸው በመስጋት
በፍርሃት ይኖራሉ። አያሳዝንም!! የተገላቢጦሽ መሆኑ !!
ወደ ዋናው ርዕሴ ልመለስ፤ እየሩሳሌም የሚገኘው ገዳማት ይዘቱ የኢትዮጵያውያን ይሁን እንጅ፤ እኔ
እስከማውቀው በ 15ተኛውና በ 16ተኛው ክፍለ ዘመን ከተገነባው የዴሬ-ሱልጣን ገዳም ጀምሮ፤የዛሬ 130
ዓመት ገደማ አጼ ሚኒሊክ አስጀምረውት አጼ ዩሃንስ ያስጨረሷት ኪዳነ ምኅረት ገዳም፤ በኢያሪኮ የሚገኘው
ገዳምና ቤት-ዓልዓዛር የተባሉት ገዳማት የሚተዳደሩት፤ የተለያዩ ነገሥታት በስማቸው ያስገነቧቸውን ህንጻዎች
ለገዳማቱና ለአገልጋይ መነኰሳቱ ይሁን በማለታቸው፤ በአሁኑ ስዓት የእሥራኤል ድምጽ ራዲዮ ጣቢያ
የሚያስተላልፍበትን የእትዬ ጣይቱ ህንጻ ጨምሮ፤የንግሥት ዘውዲቱ ህንጻ፤የአሉላ አባ ነጋ ህንጻ፤....ወዘተ
ኪራይ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ገዳማቱ የኪራይ ገቢ አላቸው። በአጭሩ የእየሩሳሌም ገዳማት
እራሳቸውን ችለው የሚስተዳድሩ ናቸው ማለት ነው። የተለያየ ከምዕመናኑ ስለት የሚሰጠውን ጨምሩበት !
ታዲያ ጫካ ቤቴ፤ ቅጠል ልብሴ፤ አውሬ ጓደኛየ ብለው ሁሉም ነገር በቃኝ፤ ዓለም ለምኔ ብለው መንነው
እንጨት ቆርጠው እሳር ነስንሰው ጐጆ ቀልሰው በዱር መሃል ኦሪታቸውን አስቀምጠው ለኢትዮጵያና ለህዝቧ
ሌት ተቀን ሱባየ ገብተው በመጸለይ ባሉት መናንያን ላይ፡ይህ እብሪተኛ!! መናንያኑ የተከለሉበትን ዱር ለስኳር
ብሎ በተደበቁበት ጫካ እርቃናቸውን ሊያጋልጥ ሲመነጥር፤ የእየሩሳሌምን መነኰሳት አይመለከታቸው
ይሆን ?!
የጻድቃን አጽም ተቆፍሮ ማዳበሪያ ሆኖ እዚያ ላይ ስኳር ሲመረት የእየሩሳሌም መነኮሳት እንደ "በጉ" ሥጋ
ተጭኖ በአይሮፕላን ሲመጣላቸው እንደሚበሉት፤ዋልድባ በጻድቃን አጽም ማዳበሪያ የተመረተውን ስኳርስ
ዝም ብለው ይጠጡት ይሆን?! አይሆንም አይባልም ይሆናል!! ዕድሜ ይስጥ ብቻ !!!
የእየሩሳሌም መነኰሳት በዋልድባና በዝቋላ ገዳም መቃጠል አይቆጫቸውም?! ምንስ ቢሆን ከአንድ ሽህ ዘመን
በፈት የተጠበቀ ቅርስ አይደለንም ?!
እሥራኤል እንኳን በምድሯ የሚገኘውን የኢትዮጵያን ሃብትና ቅርስ፤ በታሪካዊ ቅርስነት መዝግባ ምኑንም
ሳትሰርዝና ሳትደልዝ በታሪካዊነት በመጠበቅ፤ ለቱሪስቶች ከምታስጐበኛቸው ከፍተኛና ታሪካዊ ቅርስ አንዱ
የኢትዮጵያውያኑ ቅርስ ነው።
ታዲያ ይህ እኩይ፤ በገዛ ሃገሯ ያሉና ዘመናት ያስቆጠሩ ገዳማትን የእሣት ቋያ ሲለቅበት፤ ዶዘር አስገብቶ
ሲመነጥር፤ የእየሩሳሌም መነኰሳትን ግድ ያልሰጣቸው ለምን ይሆን ?!
እዚህ እሥራኤል ሃገርም እኮ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግና በደልን የማሰማት ሙሉ ነጻነት አለ!፤ እና እነዚህ
የሃይማኖት መነኰሳት ለምን ኢትዮጵያ የሚደርሰውን ሰቆቃ ማሰማት ተሳናቸው?!
እስካሁን ህዝብ ሲጨፈጭፍና ሲያፈናቅል፤ ሃገሪቱን ለቅኝ ግዛት አሳልፎ ሲሰጥ በፖለቲካ ጣልቃ አንገባም
ብለው ዝም አሉ!! እውነት ሃገር እየሞተ ዝም ማለት ያስፈልግ ነበር?!ሃገር ከሌለ ኩራት በምን ሊሆን?! በተለይ
በእሥራኤል የሚኖሩ መነኰሳት የሚያውቁትና እያንዳንዱ ይሁዲ እንዴት ሃገሩን እንደሚወድ ያያሉ!!
ይሁዳውያን ሀገር ስላልነበራቸው የደረሰባቸውን ጭፍጨፋና ውርደት ያውቃሉ። በዚህ ምክንያት በተቻላቸው
ሁሉ "ሰውን በሰውነቱ" እና በሰብዓዊነቱ መብቱ በማክበር በኩል ከፍተኛ ትኩረት ሲያደርጉ ያያሉ።
ታዲያ እነዚህ የእግዚአብሄር ባሪያና አገልጋይ ነን ብለው ከላይ እስከታች ጥቁር ቀሚስ ለብሰው፤ ጥቁር እሻሽ
!?ጠምጥመውና ጥቁር ነጠላ ደርበው ዓለም በቃን ያሉ!! እንዴት ለወገን መቆርቆር አልቻል አላቸው
ሁሉም ይቅር፤ ለሃይማኖታቸውስ አይሞቱም?! ወይስ እኛ በጥሩ ሁኔታ ስላለን ስለሌላው ግድ የለንም፤የድሉ
!?ጉዳይ ነው ማለታቸው
እስኪ ከወዲህ ከወደ እየሩሳሌም ድምጻችሁን አሰሙ?! እናንተ ብታስተባብሩን እኛ እናግዛችኋለን!! እናንተ
ባለቤቶቹ ተቀምጣችሁ እኛ ማስተባበር አንችል!!
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ዘርግታለች!!!!
ከእሥራኤል

No comments:

Post a Comment