Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Friday, 11 May 2012

ጸረ አማራነት አንድ ቀን ጸረ ህዝብነት ይሆናል!

ገረመው አራጋው | May 11th, 2012 at 1:04 am | |
ገረመው አራጋው
የጎሳ ግጭትና እልቂት ዛሬ ዛሬ ጆሮአችን እንዲያም ሲል አይናችን እየለመደ መጣና እንደሌላው ጊዜ ብዙም የሚሰቀጥጥና የሚያስፈራ ወሬ አይደለም ዛሬ ካለንበት ጊዜ ላይ የደረስነው ባለፉት አያ አመታት በተለያይ የአገራችን ክፍሎች የብሄር ግጭትና የዜጎች ከመኖሪያ ቦታቸው መፈናቀል እየሰማንና እያየን ነው የመከራ ጊዜ እረጅም ነው ይባላል ግን ደግሞ ከዚያም በላይ ሃያ አመት አጭር ጊዜ አይደለም የኢትዮያ ህዝብ ከሞትና ከእቂት ከስደትና ክፍረሃት ጋር መኖሩን በግድ እየተለማመድን ነው ማለት ይቻላል ዛሬ በሀገራችን ላይ ሌላው ቀርቶ ለሰልፍ የወጣና ለምርጫ የተነሳን ህዝብ በጥይት ማስፈራራት ማሰር መደብደብ ማሰቃየትና መግደል  አዲስ ነገር አይደለም ሞትንና እልቂትን ሁሉም ከልጅ እስከ አዋቂ እየቀመሰ ነው::
ብዙ ሰው እንዲሁ በተለምዶና  ለአፍ ብቻ ካልሆነ በስተቀር ዛሬ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚነሱትን  ግጭቶችና  ግድያዎችን ማን እንደፈጠረውና እንዳቀነባበረው መጠየቁን  ትታል የትም ይሁን የት በጎሳዎች መካከል የሚቀጣጠለው ሁከትና ግጭት በእነማን ፍላጎትና  ግፊት እንደሚካሄድ ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቀዋል በስልጠን ላይ ያለው አምባገነን የወያኔ ስርዓት ጫካ ገባሁ ሲል ጀምሮ ትግሌ ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ አማራ ነው ካለ ከዘረኛ ቡድን ሌላ ባይጠበቅም አምባገነኑ የመለስ ስርአት የአማራውን ህዝብ  ለማጥፋት ገና ከደደቢት የጀመረውን ዘመቻ ቀስ በቀስ እየፈፅመና እያስፈፅመ መሆኑን ፅሀይ የሞቀው ሀቅ ከሆነ ሰነበተ::
ወያኔ ወደስልጣን  በጠመንጃ ሀይል ከመጣ ጀምሮ የአማራን ህዝብ ማንነትና ታሪኩን ለማጥፋት የላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቆይቶአል አሁንም አጠናክሮ ቀጥሎበታል ለምሳሌ ወያኔ ወደስልጣን ከመጣ ጊዜ ጀምሮ በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸሙት ወንጀሎች;
አማራው ህዝብ ለብዙ ዘመናት ያስተዳድራቸው የነበሩትን  የጎንደርንና የወሎን ሰፋፊና ለም  መሬቶችን ወደፊት ታላቅዋን  ትግራይ ለመመስረት   ወደ እራሱ ግዛት ያጠቃለለው ወያኔ የአማራውን ህዝብ ከለም መሬቱ አፈናቅሎ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ጥገኛ እንዲሆኑ እንዲራቡ  እንዲሰደዱም አድርጎአል ይህ በዚህ ሳያንሰው ማንም የክልሉ ነዋሪ ሳያውቅና ሳይሰማ  የአማራን መሬት ለሱዳን አስረካቦል የአካባቢው ነዋሪዎች በባእድና በወያኔ ወታደሮች አስጨፍጭፋል::
በአማራው ላይ ጥቃት የተጀመረው ዛሬ ሳይሆን ከፋሽስት ኢጠሊያ ወርራ ግዜ ጀምሮ እንደነበር ታሪክ ይመሰክራል ይህንንም የባንዳነት ተግባር ወያኔ ጠመንጃ ካነሳ ጊዜ ጀምሮ በትግል ወቅትም ሆነ መንግስት ከሆነ በሃላ በግልጽና በስውር ከአፍራሽ የትግል አጋሮቹ ጋር በመሆን አያሌ ጥቃቶችን በዚህ ህዝብ ላይ ሲያካሂዱበት እንደነበር  የትናንት ትዝታችን ነው   ሆን ተብሎና በተቀነባበረ መልኩ በአርባጉጉ በምስራቅ ወለጋ በበደኖ በአረካ ወዘተ አያሌ አማሮችን ጨፍጭፋል አስጨፍጭፋል እንዚህም  የዘር ማጥፋት ድርጊቶች ክተፈጸሙ በሁዋላ የወያኔ መንግስት እንድም ግለሰብ ለፍርድ አለማቅረቡ እራሱ ወያኔ የድርጊቱ ዋነኛ ተዋናይ እንደነበረ ያረጋግጣል::
ዘሩና ታሪኩ እንዲጠፋ በወያኔ የተወሰነበት የአማራው ህዝብ እንደ ወያኔ የኢትዮጵያ ጠላት አባባል በራሱና በታሪኩ የሚተማመን አትንኩኝ ባይ ለነጻነቱ ለህልውናው ለህይማኖቱና ለሀገሩ ዳርድንበር ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር ማች በመሆኑ ነው ለማያባራ ጥቃት የተዳረገው ወያኔ ወደ ሰልጠን ከመጠበት ጊዜ ጀምሮ አማራውን ነፍጠኛ በማለት ከሌላው ጎሳ ጋር ተፋቅሮ ተጋቤቶ ተዋልዶና ተዋህዶ ከኖረበት ቀየው በግፍ ሲያባርሩት እንደነበር ከሞት የተረፉት ተፈናቃዮች ምስክር ናቸው በተለይ በሽግግሩ ዘመን በአማራው ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ታሪክ ምን ግዜም ሲያስታውሰው ይኖራል ::
በጣም የሚገርመው በአንድ ወቅት አምባገነኑ መለስ የአማራውን ህዝብ እንዳያንሰራራ አድርገን አዳክመነዋል እስክታውንና ተረቱን ይዞ ይኑር ማለቱ አይዘነጋም ይህንኑ የአለቃቸውን ቃል እንደየገደል ማሚቱ  የሚያስትጋቡ አንድ  የወያኔ ጀነራልና  ጦር መሪ የሆኑት ግለሰብ በአንድ  ስብሰባ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር  በታጋዮች የህይወት መስዋትነት በተከፈለ አካላቸውን ባጡ በትግራይ ልጆች ደም እኮ ነው ደርግን ከፍተኛ መሰዋትነት ከፍለን ከስልጣኑ አውርደነዋል አማራውንም ደግሞ እንዳያንሰራራ አድርገን አጥፍተነዋል ማለታቸውን እናስታውሳለን::
የወያኔ ድበቅ አጀንዳ አሁን ደግሞ በደቡብ ኢትዮጵያ በተለይ በቤንች ማጂ ዞን በጉራ ፈርዳ ወረዳ እራሱ ባወጣው ህገ መንግስት ውስጥ ዜጎች በፈለጉት ክልል የመኖርና ሀብት የማፍራት መብታቸውን በመጣስ  እጅግ ቁጥራቸው የበዛ የአማራ ብሄር ወገኖቻችን ላይ ከፍተኛ በደል እየተፈጸመ ይገኛል በደሉን እያስፈጸመ ያለው የአምባገነኑ የመለስ ሰርዓት በሚሰጠው መመሪያና ትህዛዝ ከክልሉ መስተዳድር ጀምሮ እስከ ወረዳ ባሉ ተላላኪዎቹ በተቀናጀ አሰራር ነው ከማፈናቀሉ ተግባር ጋር በተያያዘ የወቅቱ ትልቅ ጥያቄ የደቡብ ክልል አስተዳደር ቀደም ሲል ሆነ አሁን በተለይ የአማራ ብሐር ተወላጆችን ለበርካታ አመታት ከኖሩበት እያፈናቀለና ወደመጡበት እየመለሰ ያለው ለምንድ ነው? ለአማራ ህዝብ መብትና ጥቅም የቆምኩነኝ የሚለው አሻንጉሊቱ ብአዴንስ የክልሉ ዜጎች መፈናቀልን በመደገፍ በዝምታ የተቀበለው ለምንድን ነው?
አማራውን ከፌደራል መንግስት ስልጣን የማራቁ  ድብቅ ተልኮ ወያኔ ስልጠን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ሲያከናውነው የነበረ ረቂቁ ሴራ ለማሳካት ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም ነገር ግን ሊሳካለት አልቻለም  ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ትልቅ የህዝብ ብዛት ያላቸውን አማራንና ኦሮሞን ህዝቦች በማጋጨት እድሜአቸውን ለማርዘም ያሴሩት ሴራ ሲከሽፍባቸው ዛሬ ደግሞ ተጋብቶ ተዋልዶ ተከባብሮና ተስማምቶ በሰላም የሚኖረውን የደቡብ ኢትዮጵያ ነዋሪዎችን ሰላም በማደፍረስ ወቅታዊውን የመምህራን ጥያቄ :የህዝብ የኑሮ ውድነት: የሰባዊና ዲሞክራሲያዊ መብት መከበር ጥያቄ አቅጠጫ ለማስቀየር የተጠቀመበት እኩይ ተግባር መሆኑን  የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቀዋል::
በአማራ ህዝብ ላይ ጥላቻን መሰረት አድርገው በመካሄድ ላይ ያሉ ማንነቱንና ታሪኩን የማጥፋት ዘመቻ በአሁኑ ወቅት በጣም ተባብሰው ቀጥለዋል አማራው እንደ ህዝብ እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ላይ ጭቆናና መከራ ሁሉ ተጠያቂ ተብሎ ሲወገዝ ቆይታል ገዝው ሁሉ አማራ ተባለ እንጂ ፓለቲካቸው ለሰፊው የአማራ ህዝብ የፈየደው ብዙ አልነበረም የአማራ ህዝብ ሰፊ ነው በኢትዮጵያነቱ አምኖ ከሌሎች ብሄሮች ጋር በመሆን ታሪክ የሰራም ህዝብ ነው አምባገነኑ የመንግስት ስርዓት ይህንን እውነታ ወደጎን  በመተው የአማራን ህዝብ ማስጨፍና ማፈናቀልን ለጥቃት  ማጋለጡን ቀጥሎበታል ብዙሃኑ የአማራ ህዝብ  በማያወላዳ መልኩ ለአገር አንድነት የቆመ ነው ይህ የኢትዮጵያዊነት ስሜቱ እንደ ሀጥያትና ወንጀል ተቆጥሮበት ከተወገዘ ደግሞ እራሱን ለማዳንና መከላከል የግድ ይሆንበታል አማራን ያህል ሰፊ ህዝብ አግልሎና አውግዞ ልማት አካሂዳለው ማለት ዘበት መሆኑን አምባገነኑ የመለስ ስርአት ጠንቅቆ እንዲያውቀው ይገባል::

1 comment:

  1. Is it not to be anti-society to be anti- Amhara in the first place? The title implies a very unpalatable precedence : an evil act that is perpetrated on Amharas, will not be ant-society as long as it remains within the Amhara people. It is only when it goes beyond that it will be anti-society. It is a little out of logic and proper thought.

    ReplyDelete