ኢትዮጵያ ሀገር
ሆና ኖራለች፡፡
ለዚህ ምስክርነት
የሚሰጡ ትርጉም
ያላቸው ምሁራን
ማንሳት ይቻላል፡፡
ከውጭዎቹ ሄኔሪ
ክሲንገር፣ ሳሙኤል ሀቲንግተን፣
ዶናልድ ሌቪን፣
ሀሮልድ ማልከስ፣
ጆን አቤኒክ፣
ዶናልድ ክሩ
ሜይ፣ ሴፋሩድ
ፓውስዋንግን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ከሀገር ውስጦቹ
ምሁራን ተክለፃድቅ
መኩሪ፣ ታደሰ
ታምራት፣ መርዕድ
ወልደ አረጋይ፣
ባህሩ ዘውዴንና
ሽፈራው በቀለን
መጥቀስ ይቻላል፡፡
እነዚህና ሌሎች
ያልተዘረዘሩ ብዙ ምሁራን
ኢትዮጵያውያን በመንግሥት ስር የመተዳደር
ልምዳቸው መንግሥት
እንኳ ባይኖር
ያለመታወክ የሚቆዩ ስርዓት
ያዳበሩ ህዝቦች
እንዳደረጋቸው ያወሳሉ፡፡ በተጨማሪም በነዚህ ሁሉ
ሺህ ዓመታት
ኢትዮጵያውያን እንደ ህዝብ
ለቁጥር የሚያታክቱ
መንግሥታትን እያሳለፉ ኖረዋል፡፡
በህዝብ አዕምሮም
በታሪክ ማህደርም
ቦታ የሌላቸው
ብዙ መንግስታትና
መሪዎችም በዚህ
መሃል አልፈዋል፡፡
መንግሥታት እና መሪዎቻቸው
እንደወራጅ ውሃ ሲያልፉ
‹የማያልፈው› ህዝብ ተመልክቷቸዋል፡፡
እነዚህ የሚያልፍ
መሪዎች የሚያልፍ
ሃሳቡን
ሲጭንባት ተመልክቷል፡፡
ባብዛኛውም መሪዎቹ እነዚህን
ሃሳብ ህዝባዊ
በማድረጉ አልተሳካላቸውም፡፡
እስቲ የቅርቦቹን
ሁለት እና
የአሁኑን መንግሥታት
ሁኔታ እናንሳ፡-
አፄ ኃይለ
ሥላሴ “የተወለድኩበትን
ሐምሌ 19 አክብሩ”
አሉን፤ አከበርንላቸውም`
፡፡ “ዘውድ
የጫንኩበትን ጥቅም 23ንም
አክብሩ” አሉን፡፡
ደግመንም አከበረንላቸው፡፡
አፄ ኃይለ
ሥላሴ አለፉ፤
የሐምሌ 19 እና
የጥቅም 23 `በዓላትም`
አለፉ፤ ተረሱም፡፡
ደግሞ ደርግ
መጣ፤ “የፊውዳሉንና
የዘውዱን ስርዓት
የገረሰስኩበትን መስከረም ሁለትን
አክብሩ” አለን፤`አከበርንለትም`፡፡ ቆይቶ
ደርግ አለፈ፤
መስከረም ሁለትም
አብሮት አለፈ፤
ተረሳም፡፡ ኢህአዴግ ደግሞ
መጣ፤ “ደርግን
የገረሰስኩበትን ግንቦት 20 አክብሩ”
አለን፤ እነሆ
‹እያከበርንለት› ነው፡፡ ኢህአዴግ
ለጊዜው እንደ
አፄውና እንደ
ደርግ ስርዓት
አላለፈም፡፡ ስለዚህ ግንቦት
20ን “እያከበርን” ነው፡፡ ነገር
ግን ፍኖተ
ነፃነት ከዚህ
አዙሪት የመውጫ
ቀዳዳው መፈተሸ
እንዳለበት ታምናለች፡፡ እስካሁን ያየናቸው
በዓላት ለገዥዎች
`አከበርንላቸው` እንጂ የኛ
አድርገን በኔነት
አላከበርንም፡፡ በመሆኑም ዋናው
መፍትሄ ገንዘብ
እየከፈሉ አሊያም
እያስፈራሩ ካሜራ ፊት
አቁሞ የማያምኑትን
እንዲያወድሱ ከማድረግ ዴሞክራሲያዊና
ፍትሃዊ ስርዓት
ገንብቶ መሪዎች
ሲያልፉም ሲከበር
የሚኖር በዓል
መፍጠር ነው፡፡
No comments:
Post a Comment