Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Tuesday 29 May 2012

መታወቂያችን አማራ ስለሚል ተመርጠን ታሰርን ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ



ከሚዛን ተፈሪ ወደ ዲማ ለሥራ ስንሄድ ኬላ ላይ መታወቂያ እየተመለከቱ ሲፈትሹ መታወቂያችን ብሔር በሚለው ቦታ ላይ አማራ ስለሚል መርጠው እስር ቤት ከተቱን፡፡ ሲሉ ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ፡፡ እነዚህ እስር ቤት ቆይተን ተፈታን የሚሉ ሰዎች እንደሚሉትዲማ በጉልበትህ ሠርተህ የምታገኘው ገንዘብ አለ የሚል መረጃ ስለደረሰን ሥራ ፍለጋ በመጓዝ ላይ ነበርን፡፡ ሚዛን ተፈሪ ስንደርስ ለፍተሻ ከመኪና ውረዱ አሉን፡፡ ወርደን ለፍተሻ ዝግጁ ሆንን፡፡ መታወቂያቸው ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ጋምቤላ፣ አፋር የሚል እንዲሳፈሩ ተፈቀደላቸው፡፡ አማራ የሚለውን 16 ሰዎች ሰብስበው እናንተ እንድታልፉ አይፈቀድም ብለው ሚዛን ተፈሪ ፖሊስ መምሪያ ወሰዱን፡፡ ከዚያም እስር ቤት አስገቡን፡፡ ከዚያም ሌላ 20 አማርኛ ተናጋሪዎች ተይዘው ታሰሩ፡፡ ምን አጠፋን? ወንጀል ሳንፈጽም ለምን ታስሩናላችሁ? ብለን ስንጠይቃቸው ወደዚያ ከሄዳችሁ አደጋ ይደርስባችኋል፡፡ ወደዚያ አማራ ሄዶ እንዲሰራ አይፈቀድም ብለውናል፡፡ሲሉ ቅሬታቸውን ይገልፃሉ፡፡ትኬት ቆርጣችሁ ወደ አማራ ክልል ተመለሱ ብለው ከሦስት ቀን በኋላ የተወሰንን ሰዎችን ለቀቁን፡፡ ብዙዎቹ አሁንም በእስር ላይ ናቸው፡፡ እኛ ወደ ትውልድ መንደራችን ለመሄድ ገንዘባችንን ጨርሰናል፡፡ ብንሄድም ቦታ ስለሌለን ማረፊያ የለንም፡፡ ለዚህ ነው የቀን ሥራ ሠርተንም ጉርጓድ ቆፍረንም ህይወታችንን እንቀይራለን ብለን ጉዞ ጀምረን የነበረው፡፡ ሆኖም ግን አማራ በመሆናችን ተዘዋውረን ሠርተን እንዳንበላ ተደርገናል፡፡ሲሉ አማረዋል፡፡ በመቀጠልም ሲናገሩእኛ ታስረን መፈታት ችለናል፡፡ ዛሬም ሥራ ፍለጋ ወደ ምንፈልግበት እንድንሄድና በነፃነት ከቦታ ቦታ እንድንቀሳቀስ አልተፈቀደልንም፡፡ ህጋዊን መንገድ ትተው በእግራቸው ጫካ ለጫካ ጉዞ የጀመሩ በርካታ ሰዎች ተገላዋል፡፡ በአውሬ ተበልተዋል፡፡ ሲገደሉም በአውሬ ሲበሉም የአካባቢው ኃላፊዎች ምንም የሚሰማቸው ፀፀት የለም፡፡ ህገ ወጦች ናቸው፡፡ እንኳን ሞቱ እንኳን ተበሉ እያሉ ሲሳለቁ ይሰማል፡፡ካሉ በኋላየሚመለከተው የመንግስት አካል ጉዳዩን በጥሞና ተመልክቶ ውሳኔ ይሰጠን፡፡ ተዘዋውረን የመኖርና ሠርቶ የመብላት መብታችን እንዲከበርልን አሳውቁልን፡፡በማለት ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ የሚዛን ተፈሪ ፖሊስ መምሪያ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥበት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

No comments:

Post a Comment