Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Friday, 1 June 2012

በአዲስ አበባ የሕዝብ ት/ቤቶች በመንግስት ተወረሱ

ግንቦት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙት 117 የህዝብ ትምህርት ቤቶች መካከል 115 ያህሉ ወደ መንግስት ትምህርት ቤትነት በያዝነው ዓመት ተዘዋወሩ፡፡

በህዝብ ይተዳደሩ የነበሩ ትምህርት ቤቶች ወደ መንግስት የተዛወሩት በህብረተሰቡ ጥያቄ መሰረት መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ይግለጽ እንጂ ሕዝቡ የት እና መቼ  ጥያቄ እንዳቀረበ ያብራራው ነገር የለም፡፡

በህዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሲያስተምሩ የነበሩ መምህራንና ሰራተኞች ምድባ በአዲስ መልክ እየተዘጋጀ መሆኑንም ቢሮው በትላንትናው ዕለትበሰጠው መግለጫ አስታውቋል ;; በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው አንድ የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር አመራር አባል በሰጡት አስተያየት የሕዝብ ት/ቤቶቹ ከፍለው ለመማር ለሚችሉ ጥሩ አማራጭ ነበሩ፡፡እውነት ለመናገር ከመንግስት ት/ቤቶች የተሻለ ብቃት ያላቸውም ናቸው፡፡ መንግስት በወሰደው እርምጃ የትምህርት ጥራቱ ወደ ኃላ እንዳይመለስ ሥጋት አለኝ ብለዋል፡፡

በፈለገዮርዳኖስ ት/ቤት ተማሪ የነበረ አንድ አስተያየት ሰጪም ውሳኔው አሳዛኝ ነው ብሎታል፡፡ “ እኛ ተማሪ በነበርን ግዜ በተመጣጣኝ ክፍያ ከፍተኛ ትምህርት እናገኝ ነበር፡፡በዚህ ላይ የመንግስት ት/ቤቶች ግማሸ ቀን ሲያሰተምሩ እኛ ግን ሙሉ ቀን እንማር ነበር፡፡በየሳምንቱ ትምህርታዊ ውድድሮች ሁሉ ስለነበሩ እርስ በርስ የነበረን ፉክክር ከፍተኛ ነበር፡፡ይህ ሁሉ በመንግስት ት/ቤቶች እንዴት ማግኘት ይቻላል” ሲል ጠይቋል፡፡

No comments:

Post a Comment