Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Monday, 28 May 2012

ሲኖዶሱ የ‹ተሐድሶ› ኑፋቄ አራማጅ ያላቸውን ድርጅቶች እና ግለሰቦች አወገዘ



. ፓትርያርኩ በአቡነ ሳሙኤል ላይ የጣሉትን እገዳ ሲኖዶሱ አንሥቷል
የኢ////ያን በካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በቤተክርስቲያኒቱ ስም የራሳቸውን ፍላጎት ለማሟላት ባላቸው ዕቅድ ቀጥተኛ የኾነውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርተ ሃይማኖትና ነባር ሥርዐተ እምነት ለማዛባት፤የኑፋቄ ትምህርት አሰራጭተዋል ያላቸውን ድርጅቶች እና ግለሰቦች ተሐድሶኑፋቄ አራማጅ ሲል የውግዘት ውሳኔ ማስተላለፉን የፍትህ ምንጮች ገለፁ፡፡ ማኅበራቱ እና ግለሰቦቹ ኦርቶዶክሳዊ ሳይኾኑ ኦርቶዶክሳዊ መስለው በቤተክርስቲያኒቱ ላይ አሳይተዋል ላለው ‹‹ክብረነክ›› ጉዳይም በሕግ እንዲጠየቁ ቅዱስ ሲኖዶሱ ትእዛዝ እንደሰጠ ለማወቅ ተችሏል ፡፡ በመናፍቅነት የተወገዙት ድርጅቶች ከሣቴብርሃን፣ ማኅበረሰላማ፣ የምሥራች አገልግሎት፣ የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር፣ አንቀጸ ብርሃን፣ የእውነት ቃል አገልግሎትና ማኅበረ በኵር የሚባሉ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ቅርንጫፍ /ቤቶችን ከፍተው የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ በግለሰብ ደረጃ የሃይማኖት ሕጸጽ እንዳለባቸው በተለያዩ ሥራዎቻቸው በተገኙ ማስረጃዎች አረጋግጬባቸዋለሁ ካላቸው መካከል ደግሞ ዲያቆን ጽጌ ስጦታው፣ መጋቤ ጥበብ ሰሎሞን መኰንን፣ ዲያቆን አግዛቸው ተፈራ፣ ዲያቆን ደረጀ ገዙና ደቀመዝሙርበዛ ሰፈርህ የተባሉ ይገኙበታል፡፡ በተደጋጋሚ ለሃይማኖታዊ ጥያቄ ተፈልገው አለመቅረባቸው የተነገረባቸው የዲያቆን በጋሻው ደሳለኝ ጉዳይም በተጨማሪ ማስረጃዎች ተጠናክሮ በመጪው ዓመት የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ተጠናቆ እንዲቀርብ ሲኖዶሱ ማዘዙ ተዘግቧል፡፡ በዚሁ ስብስባ የሃይማኖት ሕጸጽ ጥቆማ የቀረበባቸው የቀድሞው የሰንበት /ቤቶች / መምሪያ ሓላፊ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደሳሙኤል ‹‹በተጠየቅኹበት ጉዳይ ያለኝ እምነት ቅዱስ ሲኖዶሱ በወሰነውና በሚወስነው ነው›› በማለታቸው ከቀረበባቸው ተጠያቂነት ነጻ እንዲኾኑ ነገር ግን እምነታቸውን በጽሑፍ ገልጸው በማቅረብ እንዲያረጋግጡ ሲኖዶሱ መወሰኑን የፍትሕ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ከአባ ሰረቀ ጋራ በውዝግብ የቆየው ማኅበረ ቅዱሳንም መተዳደሪያ ደንቡ ከወቅቱ ኹኔታ አንጻር ሊያሠራው በሚችለው መልኩ ተመርምሮ እንዲሻሻል በማስፈለጉ ከጳጳሳት፣ ከሊቃውንትና ከሕግ ዐዋቂዎች የተውጣጣ ኮሚቴ እንዲቋቋምና እስከዚያው ድረስ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ //ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾኖ አመራር በመቀበል እየሠራ እንዲቆይ መወሰኑን በሲኖዶሱ ውሳኔ ላይ ተመልክቷል፡፡ ከሚያዝያ 30 ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 15 ቀን 2004 . ድረስ 16 ቀናት ሲካሄድ የቆየው የሲኖዶሱ መደበኛ ስብሰባ ከትላንት በስትያ ከቀትር በኋላ ሲጠናቀቅ ባወጣው ባለ ዐሥር ነጥብ የአቋም መግለጫ ላይ እንደተመለከተው÷ ኅብረተሰቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ተሐድሶኑፋቄ አራማጅ ግለሰቦችና ማኅበራት ላይ ያስተላለፈውን ውግዘት በመረዳት ከአሳሳች ኑፋቄያቸው ብርቱ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡ በሲኖዶሱ የተሠየመው ጳጳሳትና የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት የተዋቀሩበት ልዩ አጥኚ ኮሚቴ የተመረመሩት ማስረጃዎች እንደሚያመለክቱት በመናፍቅነት የተወገዙት ድርጅቶችና ግለሰቦች የቤተክርስቲያኒቱን ውስጣዊ ሰላም በማናጋት ተቋማዊ አንድነቷን ለመከፋፈል፣ በኅትመት ውጤቶቻቸው የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐተ እምነት፣ ክርስቲያናዊ ትውፊትና ታሪክ በመንቀፍ፣ የጽርፈትና የነቀፋ ቃል ሲያስተላልፉ የነበሩ መኾናቸውን ለፍትሕ ጋዜጣ አስተያየታቸውን የሰጡ የጠቅላይ ቤተክህነቱ ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ‹‹ጉዳዩ የበርካታ ምእመናንና አገልጋዮች ቀልብ ስቦ የቆየ እንደመኾኑ የውሳኔው አፈጻጸምም የዚያኑ ያህል አንገብጋቢ መኾኑ አይቀርም፤›› ይላሉ ምንጮቹ፡፡ በተያያዘ ዜና ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስ የኾኑት አቡነ ሳሙኤል የኮሚሽኑን ተንቀሳቃሽና የቁጠባ ሒሳብ ከሌሎች የቤተክህነቱና የኮሚሽኑ ሓላፊዎች ጋራ በጣምራ ፊርማ እንዳያንቀሳቅሱ ለባንኮች በጻፉት ደብዳቤ ማገዳቸው ሕገ ቤተክርስቲያንን እንደሚፃረር ሲኖዶሱ ማስገንዘቡ ተጠቁሟል፤ አላግባብ የተላለፈው የፓትርያሪኩ እገዳም ተሽሮ አሠራሩ በነበረበት እንዲቀጥል ሲኖዶሱ ማዘዙ ተነግሯል፤ የኮሚሽኑ
አሠራርም አዲስ በወጣው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጀንሲ ዐዋጅ መሠረት ከቅዱስ ሲኖዶስና ከሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በተውጣጡ በድምሩ 20 አባላት በሚገኙበት ጠቅላላ ጉባኤና ዘጠኝ አባላት ባሉት ቦርድ የበላይ ተቆጣጣሪነት እንዲመራ መወሰኑን ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል፡

No comments:

Post a Comment