Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Monday 28 May 2012

ትናንት በፒያሳ አትክልት ተራ ነጋዴዎች ከፖሊሶች ጋር ተጋጩ - በግጭቱ ነጋዴዎች፣ ገዢዎችና ፖሊሶች ተጎድተዋል



በአራዳ ክፍለ ከተማ በአዲሱ ቀበሌ 02 በተለምዶ ‹‹ፒያሳ አትክልት ተራ›› ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትናንት በአከራይና ተከራይ ውል ምክንያት
በሻጮችና በፖሊሶች መካከል በተፈጠረ አለመግባባትና ግጭት ሳቢያ ሰዎች መታሰራቸውንና መጐዳታቸውን ምንጮች ለፍትሕ ገለፁ። ትናንት ከረፋዱ 530 ሰዓት ገደማ ላይ የቀበሌው መስተዳድሮች ፖሊሶችን ይዘው በስፍራው በመምጣት በመደባቸው ላይ ይሰሩ ከነበሩት አትክልት ሻጮች መካከል ቁጥራቸው 15 ያህል የሚገመቱትን ‹‹ቦታችሁን ለቃችሁ ውጡ›› የሚል ትእዛዝ እንዳቀረቡላቸው ምንጮች ለፍትሕ አስረድተዋል። ‹‹መንግስት ከወራቶች በፊት አውጥቶት በነበረው የአከራይ ተከራይ ውል ምክንያት ለሰባት ወራት ያህል ከአከራዮች ጋር ውል አቋርጠን ነበር። ቀበሌውም በእናንተ ምክንያት ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ለአከራዮች ምንም እንዳትከፍሉየሚል ሀሳብ ሰጥቶን ነበር›› የሚሉት እነዚህ ሻጮች ‹‹የቀበሌው መስተዳድር ኃላፊነት ወስዶ በሕጋዊ መንገድ ሕጋዊ ወረቀት የሚሰጠንና የሚረከበን ከሆነ እንለቃለን›› ማለታቸውን ምንጮች ይናገራሉ። በወቅቱ የቀበሌው መስተዳድር ‹‹መጀመሪያ እዚህ ስትገቡ ወረቀት ማን ሰጣችሁ? ለእናንተ ወረቀት አያስፈልጋችሁም›› ካላቸው በኋላ በመሀል ፖሊሶች አንዱን አትክልት ሻጭ በጉልበት ጎትተው መደብደብ እንደጀመሩ የዓይን እማኞች ለፍትሕ ተናግረዋል። ከዚያም ሰኢድ ሹመካ የተባለውን ልጅ ፖሊሶች ጎትተው ሲደበደቡት በስፍራው የነበረ ሕዝብ እንደጮኸባቸውና ከፖሊሶች ጋርም ሻጮች በዱላ ወደ መደባደብ እንዳመሩ እነኚህ የዓይን እማኞች ገልፀዋል።
ሰኢድም ‹‹ወደ ፖሊስ ጣቢያ አልሄድም›› በማለቱ ፖሊሶች በጋራ ጐትተው እየደበደቡት ቀበቶውን ፈትተው ሁለት እጆቹን በካቴና በማሰር የፖሊስ
መኪና ላይ እንደጫኑት ምንጮች አስረድተዋል። በዚህ ወቅትም በአካባቢ የሚገኘው የአፍሪካ አንድነት ሁለተኛ ደረጃ /ቤት ተማሪዎች በጩኸት አካባቢውን መረበሻቸውን የፍትሕ እማኞች ተናግረዋል። ከረፋዱ 530 ሰዓት የጀመረው ረብሻ ከቀኑ 730 ገደማ ማቆሙን የሚገልፁት ምንጮች ሶስት አትክልት ሻጮች፣ የተወሰኑ ገበያተኞችና ፖሊሶች ላይ ጉዳት መድረሱን፣ እንዲሁም 15 ያህል ሰዎች በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን አስረድተዋል። ፍትህ ጋዜጣም ፒያሳ አካባቢ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ የሆኑትን ኮማንደር መስፍን አያሌው ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጥያቄ አቅርባ ነበር። ሆኖም ኮማንደሩ የአራዳ /ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ የሆኑትን ኮሚሽነር እሸቱ አበበን መረጃ ለማግኘት ማስፈቀድ እንደሚኖርብን በመጥቀስ ምላሽ ሰጥተውናል፡፡ ኮሚሽነር እሸቱን ስለጉዳዩ በስልክ ካነጋገርናቸው በኋላ ‹‹ፖሊስ በአከራይ ተከራይ መመሪያ መሰረት የተወሰነውን ውሳኔ ፈፅሟል፡፡ብለውናል።

No comments:

Post a Comment