Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Friday, 1 June 2012

በከምሴ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ድዋ እንዳያደርጉ ተከለከሉ

ግንቦት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በከምሴ ልዩ  ዞን ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ሙስሊሞች ባለፈው አርብ ሶላት ሊያደርጉ በከተማዋ መሀል አደባባይ በሚገኘው መስጊድ ውስጥ  ለመሰባሰብ ጉዞ ሲጀምሩ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት አካባቢውን ተቆጣጥረዋል። ነዋሪዎቹ ከመስጊዱ ግቢ አልፈው  በአስፓልቱ ላይ በመቆማቸው የከተማው ትራፊኮች  ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ እና ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚሄዱትን መኪኖች  ጉዞአቸው እንዲያቆሙ ለማድረግ ተገደዋል።
በፌደራል ከባድ መሳሪያዎች የተከበቡት ሙስሊሞች ሶላታቸውን  እንደጨረሱ፣ ፌደራል ፖሊሶች ወደ መስጊዱ ገብተው አባረዋቸዋል። አንድ ስማቸው እንዳይጠየቅ የፈለጉ በእድሜ የገፉ አዛውንት፣ እንደተናገሩት ሙስሊሞች ከሶላት ውጭ ድዋ ወይም ስብሰባ ማካሄድ እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል። ሙስሊሞቹ ወደ ሌላ አካባቢ በመሄድ ሲሰባሰቡ ፣ የፌደራል ፖሊሶች ወደ ቦታው በመሄድ በድጋሜ እንዲበተኑ አድርገዋል።
ምንጮች እንደገለጡት በነገው ሶላት ምናልባትም ግጭት ሊነሳ ይችላል የሚልፍ ከፍተኛ ፍርሀት አለ።

No comments:

Post a Comment