Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Tuesday, 29 May 2012

በአቧሬ አድዋ አደባባይ ፊት ለፊት ተሰቅሎ የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ግዙፍ ምስል ባልታወቁ ሰዎች ተሰረቀ


 
በአቧሬ አድዋ አደባባይ ፊት ለፊት ተሰቅሎ የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ግዙፍ ምስል ባልታወቁ ሰዎች መሰረቁ ተገለፀ፡፡ በኢሳያስ ማስታወቂያ ታትሞ የተተከለው የአቶ መለስ ምስልበዘመነ ትውልድ ያልተደፈረውን አባይ የደደፈረ ጀግናየሚል መፈክር የያዘ እንደነበር የድርጅቱ ባለንብረት አቶ ኢሳያስ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ተናግሯል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደ ገለፁት ምስሉ ተተክሎ የቆየው ለአምስት ቀናት ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የምስሉን መጥፋት ግራ አጋቢ ያደረገው የአቶ መለስ ፎቶ በላዩ ላይ የታተመበት ከመሆኑ በተጨማሪ በቀን መሰረቁ ነው፡፡ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የአቶ መለስን ተክለ ስብዕና የሚገነቡ ምስሎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተበራክተዋል የሚሉት ነዋሪዎቹ በየትኛውም የአቶ መለስ ምስል ላይ ጉዳትም ሆነ ጥፋት ደርሶ እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡ አቶ ኢሳያስ ለምስሉ 35,000 (ሰላሣ አምስት ሺህ) ብር በላይ ማውጣቱን ገልጸዋል፡፡ አቶ ኢሳያስ አክሎም 28 ካሬ የሚሆነው ይህው ምስል በመጥፋቱ እንደተደናገጠ ለፍኖተ ነፃነት ተናግሯል፡፡ ይኽው የጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ምስል ከተሠቀለበት ቦታ ተገንጥሎ የተወሰደ ሲሆን በዘመናዊ ዲጂታል የህትመት መሣሪያ በኢሣያስ ማስታወቂያ ታትሞ በአቧሬ አድዋ አደባባይ ፊት ለፊት ተሰቅሎ የነበረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኢሳያስ ማስታወቂያ ባለቤት ወጣት ኢሳያስ ለፍኖተ ነፃነት እንደተናገረው የምስሉ መጠን 7 ሜትር 4 ሜትር መሆኑን በመግለፅና ስራውን ለእይታ ለማብቃትና አጠቃላይ የፍሬም ሥራውን በማካተት 35,000 (ሰላሣ አምስት ሺህ ብር) ወጭ እንደተረገበት ገልፃóል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የጠ/ሚኒስትሩ ምስል ግዙፍ ሆኖ ከፊት ለፊት አሁን በመገንባት ላይ ያለው የህዳሴው ግድብ በአንድ ላይ ሆኖ ከምስሉ ስርበዘመነ ትውልድ ያልተደፈረውን አባይ የደፈረ ጀግና

No comments:

Post a Comment