በቅርቡ በቡራዩ
ከተማ በከንቲባ
ኩማ ደመቅሳ
በተመራው ሙሰኞችን
የማጋለጥ ስብሰባ
ላይ “ወ/ሮ አዜብ
መስፍን ያለ
አግባብ በወንድማቸው
ስም መሬት
ወስደዋል” ብሎ
ያጋለጠው የማዘጋጃ
ቤቱ ሠራተኛ
መታሰር በከተማው
መነጋገሪያ መሆኑን በአካባቢው
ያነጋገርናቸው የከተማው ነዋሪዎች
ለሪፖርተራችን ገለፁ፡፡ ነዋሪዎች
እንደሚሉት “መድረኩ የተዘጋጀው
በቡራዩ አካባቢ
የመሬት ቅርምት
ተፈጽሟል፤ በመንግስትና በህዝብ መሬት
ግለሰቦች አላግባብ
በልጽገዋል፤ ከፍተኛ ሙስና
ተፈጽሟል ተብሎ
ነበር” ይላሉ፡፡
ሆኖም ግን
ይላሉ ምንጮቻችን
“የመድረክ አመራሩ ተሰብስበው
በአካባቢው ኃላፊዎችና ከቁጥር በማይገቡ
ሙሰኞች ላይ
ብቻ ጣቱን
እንዲቀስር እንዲያጋልጥ ግፊት ይደረግ
ነበር፡፡ ይህንን
የተገነዘበው አቶ ኃይሉ
ንጉሴ የተባለው
የማዘጋጃ ቤቱ
የፋይናንስ ሠራተኛ ተነስቶ
ትኩረቱን ለምን
በትንንሾቹ ብቻ ታደርጋላችሁ፡፡
ሙስናን በቁርጠኝነት
የምትታገሉ ከሆነ ወደ
ላይም አትመለከቱም፡፡
በዚህ በከተማችን ወ/ሮ አዜብ
መስፍን በወንድማቸው
ስም መሬት
ወስደዋል፡፡ ለምን አይጣራም?
ለምን እሳቸውም
አይጠየቁም” ብሎ ተናግሯል፡፡
በወቅቱ ስብሰባውን
የሚመሩት ከንቲባ
ኩማ ደመቅሳ
“ጥቆማው አንድና አንድ
ነው፡፡ ጥቆማው
በማስረጃ መረጋገጥ
አለበት፡፡ ዝም ብሎ
መጠቆም አይደለም፡፡”
እያሉ ጥቆማውን
ለማጣጣልና ለማንቋሸሽም ሞክረዋል፡፡ ይህ ሲገርመን
በቅርቡ ጠቋሚውን
በሙስና ትፈለጋለህ
ተብሎ ታስሯል፡
፡ መንግስት
በተለይ የኦሮሚያ
ክልላዊ መንግስት
ሙስናን ለመዋጋት
ያለውን ቁርጠኝነትና
ጥያቄ ውስጥ
የሚከት ከመሆኑም
በላይ በመንግስት
ላይ ያለን
እምነት እየተሸረሸረ
ነው፡፡” ሲሉ
ሥጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ አቶ ኃይሉ
ንጉሴ በገፈርሳ
ቡራዩ ውስጥ
ሊቀመንበር ሆኖ ያገለገለ
ሲሆን በአሁኑ
ወቅት በቡራዩ
ማዘጋጃ ቤት
የፋይናንስ ሠራተኛ ነበር
ወ/ሮ
አዜብ መስፍን
በአሁኑ ጊዜ
በአገራችን ያለአግባብ ከፍተኛ ሀብት
አፍርተዋል ተብሎ ከሚታሙት
ግለሰቦች ውስጥ
አንዷ መሆናቸው
ይታወቃል፡፡
No comments:
Post a Comment