Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Thursday, 31 May 2012

የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጅፀደቀ

በኢንተርኔት ሰልክ መደወል እሰክ 8 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሰራት ያስቀጣል
ከኢኮኖሚያዊ ኪሣራ ባሻገር የአገሪቱን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ስጋት ሆኗል በተባለው የቴሌኮም ማጭበርበር ላይ የወጣው ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከትናንት በስቲያ ያፀደቀው ረቂቅ አዋጅ እንደሚያመለክተው፤ ከኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ፈቃድ ውጪ ማንኛውንም አይነት የቴሌኮሚኒኬሽን መሣሪያ ማምረት፣ መገጣጠም፣ ከውጭ ሀገር ማስመጣት፣ መሸጥ እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና እስከ 150ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ያስቀጣል፡፡ በፀረሽብርተኝነት አዋጅ ከሚያስቀጣ ወንጀል ጋር የተያያዘ ሽብር የሚያስከትል መልዕክት ለማሰራጨት ወይም በወንጀል ህግ የሚያስቀጣ አስነዋሪ መልዕክቶችን ለማሰራጨት በማንኛውም የቴሌኮሙኒኬሽን መሣሪያና ኔትወርክ መጠቀም እስከ ስምንት ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራትና እስከ 80 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ያስቀጣል፡፡
ምክር ቤቱ ያፀደቀው አዲሱ አዋጅ፤ ኢንተርኔትን በመጠቀም የስልክ ጥሪ ወይም የፋክስ አገልግሎት የሚሰጥ ማንኛውንም ሰው በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ከ3 ዓመት እስከ ስምንት አመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና በስልክ ጥሪዎቹ ሊያገኝ ይችላል ተብሎ የሚገመተውን ገቢ አምስት እጥፍ በሚሆን መቀጫ ይቀጣል፡፡ በኢንተርኔት ስልክ በመደወል ተግባር ላይ የተሳተፈ ወይንም የስልክ ግንኙነቱን ያደረገው ሰው ደግሞ እስከ 2 ዓመት በሚደርስ እስራትና እስከ ብር 20ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ይወሰንበታል፡፡ ፍርድ ቤት በጥፋተኞቹ ላይ ቅጣት በሚወስንበት ወቅት ወንጀሉን ለመፈፀም በጥቅም ላይ የዋለ ማንኛውም የቴሌኮሙኒኬሽን መሣሪያ በመንግስት እንዲወረስ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ በፀደቀው አዋጅ መሰረት፤ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀሎች የመጀመሪያ ደረጃ የመዳኘት ሥልጣን የሚኖረው የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሲሆን የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀሉ ለመፈፀሙ ወይም ሊፈፀም ለመሆኑ ፖሊስ ካመነ በድብቅ የሚደረግ የብርበራ ማዘዣ ፈቃድ ከፍርድ ቤት አውጥቶ ለመበርበር እንዲችል ስልጣን ሰጥቷል፡፡ በህገወጥ መንገድ ሲምካርድ፣ ክሬዲት ካርድ፣ የደንበኞች መለያ ቁጥር ወይም ዳታ  የሚሰራ ወይም የሚያባዛ ወይም በህገወጥ መንገድ የተባዙትን ሲም ካርዶች፣ የደንበኞች መለያ ቁጥሮች ወይም ዳታዎች የሚሸጥ ወይም በማናቸውም መንገድ የሚያሰራጭ ማንኛውም ሰው በወንጀሉ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ፤ እስከ አስራ አምስት ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራትና 150ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ያስቀጣል፡፡ የቴሌኮም የማጭበርበር ወንጀል የብሔራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥልና ዜጐች በመንግስታቸው ላይ አመኔታ እንዲያጡ የሚያደርግ ከባድ ወንጀል መሆኑን የጠቀሰው አዋጁ ፤ወንጀሉ ለተለያዩ የሽብር ሃይሎች መጠቀሚያ መሆኑን፤ አሠራሩ ለሙስናና ብልሹ አሠራር የተጋለጠ እንዲሆን በማድረግ ተደራራቢ ወንጀሎች የሚፈፀሙበት እጅግ ሥር የሰደደ አደጋ እንደሆነ ገልጿል፡፡
አለም አቀፍ የስልክ ጥሪዎችን የአገር ውስጥ በማስመሰል (ኮልባክ) ወንጀል በየዓመቱ በበርካታ ሚሊዮን የሚገመት የውጭ ምንዛሪ አገሪቱ እንድታጣ እያደረጋት መሆኑን የጠቆመው አዋጁ፤   በወንጀሉ ተሳታፊ የሆኑትን እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲሁም በአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑ ሰዎች እስከ 2 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ይደነግጋል፡፡ ህገወጥ የቴሌኮም መሣሪያዎችን በሲስተሙ ላይ በመግጠም ድርጅቱ በአንድ የስልክ ጥሪ ማግኘት ከሚገባው ገቢ 83 በመቶ ያስቀራል በተባለውና ህገወጥ የቴሌኮም መሳሪያዎችን ከውጭ በማስገባት ከአገሪቱ የቴሌ ሲስተም ሳይገናኝ ራሱን የቻለ የቴሌኮሙኒኬሽን ሲስተም ለመፍጠር ያስችላሉ የተባሉት ወንጀሎች በአዋጁ በአደገኝነታቸው ከተለዩ ወንጀሎች መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡

No comments:

Post a Comment